ምንም እንኳን ፍ/ቤቱ ለጉብኝት ዩተዘጋጅ የጉብኝት ቀን ባይኖረውም  ማንኛውም  ጎብኝ ወደ ፍ/ቤት መጥቶ  የተለያዩ የችሎት ስነ ስረዓቶችን መከታተል ይችላሉ፡፡  እባከዎ ለጉብኝት ወደ ፍ/ቤቱ ሲመጡ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የስራ ስዓት ብቻ ይምጡ፡፡

የፍ/ቤቱ የስራ ቀናት፡ ከሰኞ -ዓርብ

የስራ ስዓት ጠዋት 2፡30-6፡30

ከሰዓት 7፡30 – 11፡30

ፍ/ቤቱ ዝግ የሚሆንባቸው ቀናት፡  ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የብሄራዊ  በዓላት ቀን ዝግ ነው፡፡

ምስክርነት በዳኝነት ዘርፍ አንድ ሰው ክርክር በሚደረግበት  ጉዳይ ላይ  ያየውን  የሰማውን እና የሚያውቀውን  እውነት የመግለጽ ወይም የማስረዳት ተግባር ነው፡፡ የምስክርነት ቃሉን እንዲሰጥ ትዕዛዝ የደረሰው ማንኛውም ሰው  ወይም ተቋም  ፍርድ ቤት በጥሪው ትዕዛዝ ላይ በወሰነው ቀነ ቀጠሮ እና ስፍራ ቀርቦ ቃሉን የመስጠት ወይም የጽሁፍ ማስረጃ የማቅረብ ሃላፊነት አለበት፡፡

ምስክር መሆኔን የማወቀው በችሎት በታዘዘው መሰረት መጥሪያ ሲደርሰኝ ነው፡፡ ፍ/ቤቱ ሌላ ትዕዛዝ ካልሰጠ በቀር ለምስክርነት ተጠርቶ የቀረበ ማንኛውም ሰው  ቃሉን እስኪሰጥ ድረስደ በየ ቃነ ቀጠሮው  መቅረብ አለበት፡፡

ለምስክርነት የመጥሪያ ትዕዛዝ ደርሶት  ሳይቀርብ የቀረው ሰው  በህግ በማይደገፍ ወይም በቂ ባልሆነ ምክንያት  ከሆነ ወይም መጥሪያው እንዳይደርሰው ሆን ተብሎ  የተሰወረ መሆኑን ፍ/ቤቱ ከተረዳ ነተጠሪው ምሰክር  ተይዞ ወይም ታስሮ እንዲቀርብ  ሊደረግ ይችላል፡፡

 በመጀመሪያ ምስክሩ እራሱ  በአካል ፍ/ቤት ቀርቦ  በችሎት ውስጥ  የሚያውቀውን እውነት  መግለጽ ወይም በትዕዛዝ መሰረት ማስረጃውን  ይዞ የሚቀርብበት ሲሆን  ሁለተኛው መንገድ ደግሞ  በችሎት የሚሰጥበት ትዕዛዝ ተከትሎ ተፈላጊውን ማስረጃ  ለፍ/ቤቱ በተለያ ዜዴዎች  እንዲደርስ  በማድረግ ይሆናል፡፡

ፍ/ቤት ቀርቦ የምስክርነት ቃል የሚሰጥደ ማንኛውም ሰው  የምስክር ኪሳራ እና አበል እንዲከፈለው  በፍ/ቤቱ ሊታዘዝለት ይችላል፡፡

ለምስክርነት የተጠራ  ማንኛውም ሰው በጉዳዩ ላይ በአቃሉን እነ ዲሰጥ ይጠበቃል፡፡ስለዚህ ፍ/ቤቱ  ምስክሩ የሰጠውን ቃል  እውነታነት የሌለው መሆኑን በተረዳ ጊዜ  በምስክሩ ላይ ቃጣት ሊጥልደ ይችላል፡፡

 በዋግ ኽምራ ከፍ/ፍ/ቤት  ባለጉዳዮች /የህግ ባለሙያዎች ስለፍ/ቤቱ  ስነ-ስርዓት ፡ መዝገብ አከፋፈት፡እንዲሁም ሌሎች ከፍ/ቤቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን  መረጃ ጥያቄዎች ከሬጅስትራሮች ማግኘት ይችላሉ፡፡

ባለጉዳዮች/የህግ ባለሙያዎች ከከፍ/ቤቱ ሬጅስትራሮች ፡

  1. ስለ ፍ/ቤቱ ስነስርዓት እና አሰራር ስለፍ/ቤት ክፍያ እና የክፍያ መጠን አዲስ ፋይል ለመክፈት  የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ወይም  የተዘጉ ፋይሎችን እንደገና ለመክፈት  የሚስፈልጉ መረጃዎች  እና የቀጠሮ ለውጥ የተመለከቱ ጥያቄዎችን በማቅረብ  አስፈላጊውን መረጃ መቅረብ ይችላሉ፡፡

  2. የፍ/ቤቱን ድረ ገጽ  በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ  ስለ መዘገብ አከፋፈት  ስለ ፍ/ቤት ችሎት ስነ ስራዓት ቀጥታ ችሎቱን በቀጥታ ስርጭት መከታተል እለታዊ እና የወደፊት መረሃ ግብሮችን ማወቅ መዝገበውን መከታተል ወ.ዘተ ይችላሉ

  1. አቤቱታ አቅራቢው አቤቱታውን ህግ በፈቀደ ጊዜ ውስጥ  ለፍ/ቤቱ የማቅረብ መብት አለው  ::

  2. ክስን/ክርክርን የመክፈት እና የመጀመር መብት ያለው አቤቱታ አቅራቢው ነው፡፡

  3. ከተከራካሪዎቹ ማንኛውም ወገን  ማብራሪያ በሚፈልገው ጉዳይ  ላይ ፍ/ቤቱ  እንዲጠይቅለት ማመልከት ይችላል :: ተከራካሪ ወገኖች በከፊል ወይም ሙሉ ላመኑበት አካራካሪ ጉዳይ ዳኝነት ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡

  4. ፍ/ቤቱ ለሚያቃርብለት ጥያቄ እውነተኛ ቃል መስጠት አለባቸው ፡፡ ነገር ግን ሀሰተኛ ቃል የሰጠ ተከራካሪ ቢኖር ማንኛውም ተከራካሪ ወገን ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆነ  በወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት አስተማሪ ቅጣት  ፍ/ቤቱ ሊጥልበት ይችላል፡፡

ጉዳዮትን ከሚመለከት ችሎት ጋር በቀጠሮዎ ቀን መገናኘት የሚችሉ  ሲሆን ከቀጠሮ ቀን በፊት  በሬጅስትራር በኩል አቤቱታ /ማስፈቀጃ/በማቅረብ ከችሎቱ በሚሰጥ ትዕዛዝ  ወይም ፈቃድ ከችሎቱ  ጋር መገናኘት ይችላሉ፡፡

የተላከለዎትን መጥሪያ መቀበል፡ በመጥሪያው ላይ በተጠቀሰው ቀን ፡ ስዓት እና ችሎት መቅረብ፡፡

ተከራካሪ ወገኖች ውስጥ  አንዱ ችሎቱ የሚካሄድበሀትን ቋንቋ የማይናገሩ ከሆነ  ፍ/ቤቱ አስተርጓሚ እንዲያቆምላቸው  የመጠየቅ  መብት እንዳላቸው  በኢፌደሪ  ህገ መንግስት አንቀጽ 20 ተደንግጓል::

ተከራካሪ ወገኖች ችሎት ላይ ሲቀርቡ በተቻላቸው መጠን መደበኛ/በማህበረሰቡ ውስጥ ቅቡልነት ያለው ልብስ/ ለብሰው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

ፍ/ቤቱ በልዩ ሁኔታ ከከለከላቸው  ችሎቶች በቀር ሁሉም የችሎት ስነ ስራዓቶች ለጎብኝ  ክፍት ነው፡፡  ማንኛውም ሰው በየትኞቹ የችሎት ስነ ስራዓቶች መካፈል እንደፈለጉ  ከሪጅስተራር ወይም ከችሎት  አስተባባሪዎች  መረጃ በመጤቅ ችሎቶቹን መከታተል ይችላሉ ወይም በድረ ገጽ አማካኝነት በስልከዎ  ቀጥታ ችሎት የሚለውን ማስፈንጠሪያ  በመጫን  ችሎቱን መከታተል ይችላሉ::

  1. ወደ ፍ/ቤት ችሎት ሲገቡ ለፍተሻ ተባባሪ መሆን/መፈተሸ/

  2. የሞባይለዎን ድምጽ ሳይለንት ማድረግ መቻል

  3. ችሎት ገብተው የሚከታተሉ ከሆነ ተገቢውን አለባበስ ይልበሱ፡፡ ባርኔጣ ወይም ራስ ላይ የሚደረጉ ልብሶች ሃይማኖታዊ ይዘት ከሌላቸው በስተቀር  ማድረግ አይፈቀድም፡፡

  4. የጽሃይደ መነጸር ካደረጉ ችሎት ሲገቡ ያወልቁ/በሃኪም ካልታዘዙበስተቀር/

  5. ችሎት ውስጥደ መቆም የተከለከለ ነው፡ እንደገቡ መቀመጫ ፈልገው ይቀመጡ፡ መቀመጫ ወንበር ለማግኘት ቀድመው ይምጡ

  6. ምግብ ፡ መጠጥ እና ማሰቲካ ማኘክ የተከለከለ ነው፡፡ በችሎት ውስጥም ሆነ በችሎት ውጭ ሲጋራ ማጨስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

  7. በችሎት ውስጥ ፎቶ ግራፍ ወይም ቪዲዮ ማንሳት የተከለከለ ነው፡፡

የዋግ ኽምራ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት  ነጻ የህግ ምክክር  አገልግሎት  ተቋም ባይኖረውም  ባለጉዳይ በወንጀል ተጠርጥሮ ችሎት ላይ ቢቀርብ  ጠበቃ ለማቆም አቅም እንደሌለው/ላት  ካስረዳ/ካስረዳች እንዲሁም ችሎቱ ከተቀበለው  የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ ሊመደብለት ይችላል፡፡